Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፋዊ የደኅንነት ሁኔታ ለኢትዮጵያ ደኅንነት ያለው አንድምታ ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ወቅታዊ፣ ዓለም አቀፋዊ እና ቀጣናዊ ጅኦ ፓለቲካ እና የደኅንነት ሁኔታ በኢትዮጵያ ደኅንነት ላይ ያለው አንድምታ ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው።

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ኃላፊ ብርጋዴር ጄነራል ቡልቴ ታደሠ በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ÷ ውይይቱ በወቅታዊ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጂኦ ፓለቲካዊ እና የደኅንነት ጉዳዮችን በጥናት እና ምርምር ደግፎ ለማሳየት በሚደረገው ጥረት ኃላፊነትን ለመወጣት ያለመ ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም የሀገርን ደኅንነት በዘላቂነት ለማስጠበቅ በሚሠራው ሥራ ተቋማዊ ኃላፊነት ለመወጣት ያለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በውይይቱ የግብፅ እና የናይል ፖሊሲ እና እስትራቴጂ፣ የአፍሪካ ቀንድ ጂኦ ፖለቲካ ሽኩቻ ፈተናዎች እና ስጋቶች፣ የሩሲያ ዩክሬን ግጭት በኢትዮጵያ ላይ የሚኖረው አንድምታ የሚሉ ሦስት ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበዋል፡፡

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ባዘጋጀው ውይይ ላይ÷ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ ጄነራል መኮንኖች፣ ዲፕሎማቶች፣ የጸጥታ እና የደኅንነት ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ነው፡፡

በለይኩን ዓለም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.