Fana: At a Speed of Life!

ትናንት በተከሰቱ ሦስት የእሳት አደጋዎች በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ እና ሸገር ከተሞች በትናንትናው ዕለት በተከሰቱ ሦስት የእሳት አደጋዎች በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ።

የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፀው÷ ትናንት ምሽት 4 ሰዓት ከ58 ላይ ባለ ሰባት ወለል ሕንጻ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ከ60 ሚሊየን ብር በላይ የተገመተ ንብረት ወድሟል፡፡

በኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ አደጋው በ10 ሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሱን እና ከእነዚህ ውስጥ ሦስቱ የእሳት አደጋ ሠራተኞች መሆናቸውን ገልፀዋል።

የእሳት አደጋዎቹን ለመቆጣጠር 8 የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና 2 አምቡላንስ ከ65 የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ጋር መሠማራቱ ነው የተጠቆመው።

በሌላ በኩል ምሽት 3 ሰዓት ከ55 በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አስኮ መናኸሪያ በሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 1ሚሊየን ብር የተገመተ ንብረት ወድሟል።

እንዲሁም ትናንት ከቀኑ 10 ሰዓት ከ46 ላይ በሸገር ከተማ ቡራዩ በሹፋን ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ከ300 ሺህ ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት ወድሟል፡፡

አደጋዎቹን ለመቆጣጠር በተደረገ ጥረት ከ250ሚሊየን ብር በላይ የተገመተ ንብረት ማዳን መቻሉ ተመልክቷል።

በዮሐንስ ደርበው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.