Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመላው ሀገሪቱ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ከተውጣጡ የዩኒቨርስቲ ምሁራን ጋር “ለሀገር ብልጽግና፤ የምሁራን ሚና” በሚል ርዕስ ተወያዩ።

ተሳታፊዎች በመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ እንዲሁም በሀገራዊ ልማት፣ ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችን አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ምሁራኑ በተሻለ ደረጃ እንድትገኝ የሚመኟትን ሀገር ለመገንባት አስፈላጊውን ርብርብ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አመላክተዋል።

ኢትዮጵያ እያጋጠሟት ያሉትን የተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች በመገንዘብ ፍላጎቶቻቸውን ከነባራዊ ሁኔታዎች ጋር በማጣጣም እና የበሰሉ መፍትሄዎችን በማፍለቅ የበለጠ ሚና እንዲጫወቱ አስገንዝበዋል።

በተሳታፊዎች የተነሱ አንኳር ጉዳዮችን በተመለከተም የሚመለከታቸው አካላት ክትትል እንዲያደርጉ አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

መጪውን ትውልድ ጠቃሚ በሚሆንበት መልክ እና ደረጃ ኮትኩቶ በማሳደግ ለሀገር አገልግሎት በማብቃት ረገድ የምሁራን ሚና ወሳኝ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገልጸዋል፡፡

ሁሉም የዩኒቨርሲቲ ምሁራን በዚህ ኃላፊነት የበኩላቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል፡፡

ለሀገራዊ ፈተናዎች ተጨባጭ መፍትሄዎችን ለማምጣት ይቻል ዘንድ እውነተኛ ምሁራዊነትን መተግበር ከምሁራን ይጠበቃል ነው ያሉት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.