Fana: At a Speed of Life!

አንበሳ የከተማ አውቶቡስ እና ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት ተዋሃዱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አንበሳ የከተማ አውቶቡስ እና ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት የአዲስ አበባ ከተማ የአውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ተብለው በአንድ ተቋም ተዋሃዱ፡፡
 
የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ግዛው አለሙ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷አውቶቡሶቹ የተዋሃዱት በተናጠል በሚሰሩበት ወቅት የሚፈጠርን የሃብት ብክነት ለመቀነሰ በማለም ነው፡፡
 
በተለይም ተቋማቱ ተመሳሳይ አገልግሎት እየሰጡ በየተለያየ የነዳጅ ዴፖ፣ የመለዋወጫ ማዕከል፣ የሰው ሃይል እና ሌሎች አገልግሎቶችን መጠቀማቸው ከፍተኛ የሃብት ብክነት ማስከተሉን ጠቁመዋል፡፡
 
ከዚህ ባለፈም ውህደቱ አውቶቡሶቹ በመዲናዋ በሚሰጡት የትራንስፖርት አገልግሎት ስምሪት ላይ የሚፈጠርን አላስፈላጊ ድግግሞሽ በማስቀረት የተሳላጠ ትራንስፖርት መስጠት የሚያስችል መሆኑን አንስተዋል፡፡
 
ስለሆነም በተበጣጠሰ መልኩ አገልግሎት ይሰጡ የነበሩት አንበሳ እና ሸገር አውቶቡሶች የአዲስ አበባ ከተማ የአውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ተብለው መዋሃዳቸውን አረጋግጠዋል፡፡
 
በመላኩ ገድፍ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.