Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ የሚኒስትሮችን ሹመት መርምሮ አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እያካሄደ ባለው መደበኛ ስብሰባ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቀረበለትን የሚኒስትሮች ሹመት መርምሮ አፅድቋል፡፡

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው።

በስብሰባውም የምክር ቤቱን 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባዔ እና የሚኒስትሮችን ሹመት መርምሮ አፅድቋል፡፡

በዚህ መሰረት፡- 1. አለሙ ስሜ – የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር

2. ሀብታሙ ተገኝ – የማዕድን ሚኒስትር

3. ግርማ አመንቴ – የግብርና ሚኒስትር እንዲሆኑ የቀረበለትን ሹመት አፅድቋል፡፡

ተሿሚዎችም በጉባዔው ፊት ቀርበው የተጣለባቸው ኃላፊነት እንደሚወጡ ቃለ-መሃላ ፈጽመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.