Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀልን ለመከላከል ያለመ የውይይት መድረክ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል በሰው መነገድና ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከል ያለመ የውይይት መድረክ በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል።

በውይይት መድረኩ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳና በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ ዲላሞ ኦቶሬ ተገኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት÷ ከችግሩ ስፋት አንጻር ሁሉንም አካላት ያሳተፈ፣ በእቅድ የሚመራና ዘላቂነት ያለው የመፍትሔ አቅጣጫ አስቀምጦ መንቀሳቀስን ይጠይቃል።

የንቅናቄ መድረኩ የቀጣይ ጊዜያትን ግቦች፣ ዋና ዋና ተግባራትና የማስፈጸሚያ ስልቶችና እቅድን ያስቀምጣል መባሉን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.