Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 6 ወራት ለ43 ብሮድካስተሮች ፈቃድ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባለፉት ሥድስት ወራት ለ43 ብሮድካስተሮች ፈቃድ መስጠቱን አስታወቀ፡፡

በባለሥልጣኑ ፈቃድ ከተሰጣቸው 43 ብሮድካስተሮች ውስጥ 34ቱ የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን ሲሆኑ÷ ዘጠኙ ደግሞ የማህበረሰብ መገናኛ ብዙኃን ናቸው፡፡

ባለሥልጣኑ የሥድስት ወራት የእቅድ አፈፃፀጸሙን ገምግሟል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር መሐመድ እድሪስ በዚሁ ወቅት በተቋሙ ባለፉት ሥድስት ወራት የተሠሩ ሥራዎች አበረታች እና የተሻለ አፈፃጸም የታየባቸው ናቸው ማለታቸውን ከባለሥልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.