Fana: At a Speed of Life!

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ያካሄደውን የሪፎርም ስራ ተከትሎ ገቢውን በከፍተኛ መጠን ማሳደግ መቻሉን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ያካሄደውን የሪፎርም ስራ ተከትሎ ገቢውን በከፍተኛ መጠን ማሳደግ መቻሉን አስታወቀ።

የኮርፖሬኑ የ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ የተካሄደበት መድረክ ዛሬ ሲጠናቀቅ እንደተመለከተው፥ በግማሽ ዓመቱ ያገኘው ገቢ ከዛሬ አምስት ዓመት በፊት ሪፎርም ሲጀመር ከነበረበት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከስምንት እጥፍ በላይ እድገት ብልጫ አለው።

በቤት አስተዳደር፣ በቤት ልማት፣ በግንባታ ግብዓት፣ በኮርፖሬት ሰርቪስ ዘርፍ እና በስትራቴጅክ የሥራ ክፍሎች በኩል በሪፎርምና በተቋም ግንባታው የተገኙ ስኬቶችን ያስቀጠሉ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸው ተጠቅሷል።

በቤት ልማት ረገድ መካከለኛውን የህብረተሰብ ክፍል ታሳቢ ያደረጉ ሁለት አዳዲስ ሳይቶችን ግንባታ መጀመሩ የተጠቆመ ሲሆን፥ በአጭር ጊዜ ተገንብተው የተጠናቀቁት ዘመናዊ አፓርትመንት ሕንጻዎችን ወደ ሥራ ማስገባት መቻሉ ተነስቷል።

ከሕገወጦች ለመጠበቅ በታቀደው መሰረት የኮርፖሬሽኑ የሆኑ ሰፋፊ ይዞታዎችን በማስመለስ ውጤታማ ስራ አከናውኛለሁም ነው ያለው።

በርካታ የመንግስት ተቋማት ቢሮዎችን የማዛመንና የማደስ ሥራ ለማከናወን ኮርፖሬሽኑ ውል ገብቶ እየሰራ መሆኑ መገለፁንም ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ይህም ዘርፉ ከፍተኛ ገቢ ማግኛ አማራጭ እየሆነ በመምጣቱ እና ተቋሙ በዚሁ ዘርፍ ተፈላጊነቱ በመጨመሩ ሥራውን በከፍተኛ ብቃት እንደሚወጣ  የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማል በመድረኩ አስታውቀዋል።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.