Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከአራት ሀገራት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከአራት ሀገራት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር የ”ኢንተር ዲሲፕሊነሪ ፖሊሲ ኦሬንትድ ሪሰርች ኦን አፍሪካ” የሚባል ፕሮጀክት በጋራ ለመስራት በኮትዲቯር አቢጃን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡

ፕሮጀክቱን አስመልክቶ በኮትዲቫር አቢጃን የአራትዮሽ ስምምነት ውይይት እየተካሄደ መሆኑ ታውቋል፡፡

በውይይቱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሐናን ጨምሮ የፈረንሳይ ቦርዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት፣ የኮትዲቫር ፌሊክስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት እና የሞሮኮ ራቫት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ተገኝተዋል፡፡

የ”ኢንተር ዲሲፕሊነሪ ፖሊሲ ኦሬንትድ ሪሰርች ኦን አፍሪካ” ፕሮጀክት በፈረንሳይ ዩኒቨርሲቲ ቦርዶ የሚደገፍ እና ፖሊሲን ያማከለ አለማቀፍ እና ጥናታዊ የምርምር መድረኮችን የሚያዘጋጅ ፕሮግራም ነው።

ለፕሮጀክቶችም ከ8 ሚሊየን ዩሮ በላይ ወጪ እንደሚደረግ ተገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.