Fana: At a Speed of Life!

የማረሚያ ቤት ኮሚሽነሮች የጋራ ጉባዔ እይተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 15 ኛው የፌደራልና የክልል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽነሮች የጋራ ጉባዔ  በሐረር እየተካሄደ ነው፡፡

የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሺነር ጀነራል ዳመና ዳሮታ በጉባዔው እንዳሉት ÷ ማረሚያ ቤቶች የሕግ ታራሚዎችን በማነፅ  የተጀመረውን ሀገራዊ ለውጥ ለማገዝ እየሠሩ ይገኛሉ።

ማረሚያ ቤቶች በቀደመው ሥርዓት የነበራቸውን አሠራር እንዲያሻሽሉ በርካታ የሪፎርም ሥራዎች መከናወናቸውንም ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም የታራሚዎችን ጥያቄዎች ለመመለስ በሀገሪቱ የሚገኙ ማረሚያ ቤቶች ደረጃቸውን የጠበቁ ለማድረግ እንደሚሠራም ጠቁመዋል፡፡

የሐረሪ  ክልል ርዕሰ መስተዳደር ኦርዲን በድሪ በጉባዔው ላይ እንደገለጹት÷ በክልሉ የማረሚያ ቤቶችን ደረጃ ለማሳደግ ከፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ጋር በትብብር እንሠራለን።

ይህም የታረመ እና አምራች ዜጋን ለመፍጠር በምናደርገው ጥረት ላይ የማይተካ ሚና ይጫወታሉ ነው ያሉት።

ለሦስት ቀን በሚቆው ጉባዔ ላይ በ14 ኛው የጋራ ጉባዔ የተላለፈ ውሳኔ ላይ ምክክር እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡

በኢዮናዳብ አንዱዓለም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.