Fana: At a Speed of Life!

ረጅም እድሜና ጤናማ ህይወት የመኖር ምስጢር

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ረጅም እድሜና ጤናማ ህይወት ለመኖር የሰው ልጅ የተለያዩ የህይወት ዘይቤዎችን ይተገብራል፡፡

ጤናማ ህይወትን ለመምራት ከሚመረጡ ዘዴዎች መካከል የአመጋገብ ስርዓትን ማስተካከል አንዱና ዋነኛው ነው፡፡

አትክልትና ፍራፍሬዎች መመገብ – እነዚህ የምግብ አይነቶች በውስጣቸው የካሎሪ መጠን አነስተኛ መሆን እንዲሁም በአሰርና (ፋይበር) የተለያዩ ንጥረ ነገሮች መሞላታቸው ለጤና ተመራጭ ያደርጋቸዋል።

በምግብ ገበታዎ ላይ አነስተኛ የጨው መጠንን አድርጎ መመገብ የደም ግፊት ተጋላጭነትን ይቀንሳል።

በካልሺየም የበለፀጉ ምግቦች – የአጥንት መሳሳት ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ቢሆንም በተቻለ መጠን ጉዳቱን ለመከላከል በካልሺየም የበለፀጉ ምግቦችን ማዘውተር ጠቀሜታው ከፍ ያለ ነው።

ቡና – የስኳር ህመም ተጋላጭነትን ከመቀነስ ባለፈ ቡናን ሳይበዛ መጠጣት ከእድሜ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች እንዳይከሰቱ እንደሚያደርግ ጥናቶች ያመለክታሉ።

ቲማቲም ፥ በአሰር እና በቫይታሚኖች የበለፀገ ስለሆነ እና ካንሰርን የመከላከል አቅም ስላለው ለጤናማ እና ረጅም እድሜ ተመራጭ ያደርገዋል።

ሶያ – ከፍተኛ የሆነ የፕሮቲን ምንጭ የሆነው ሶያ ስጋን እና ሌሎች የፕሮቲን ምንጮችን የሚተካ በተፈጥሮ አትክልት የሆነ ምግብም ነው።

የታሸጉ ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ – የተቀነባበሩ ምግቦች ብዙውን ጊዜ ተወዳጅ ናቸው ፤ ሆኖም የካሎሪ መጠናቸው ከፍተኛ በመሆኑ ለአላስፈላጊ ውፍረት፣ ለልብ ችግር፣ ለስኳርና የተለያዩ በሽታዎች ያጋልጣሉ፡፡

በዚህም የታሸጉ ምግቦችን ከመመገብ በመቆጠብ ጤናማ ህይወትን መምራት ያስፈልጋል፡፡

አሣ – ዓሣ ከፍተኛ ጥራት ያለው ፕሮቲን እና ጤናማ የሆነ ስብ እንዲኖር ያደርጋል፡፡

ጥናቶች እንደሚያሳዩት አሣን አዘውትረው የሚመገቡ ሰዎች የልብ ህመም፣ የመርሳት በሽታ እና የአንጀት እብጠት በሽታዎችን ጨምሮ ለተለያዩ በሽታዎች የመጋለጥ እድላቸው ዝቅተኛ ነው።

በቂ እንቅልፍ ማግኘት – ለጤናማ እና የተረጋጋ ህይወት ለመምራት አስፈላጊ እንደሆነ ይነገራል፡፡

ሆኖም በቂ እንቅልፍ የማያገኙ ሰዎች የአካል እና የአዕምሮ ብቃትን በመቀነስ ድብርት፣ ድካምን ጨምሮ ለአላስፈላጊ ውፍረት እንደሚጋለጡ ጥናቶች ያመላክታሉ።

ውሃ በልኩ መጠጣት – ከካሎሪ፣ ከስኳር እና ከተጨማሪ ነገሮች የጸዳ በመሆኑ ጤናማ ህይወትን ለመምራት ምርጡ መንገድ ነው ሲሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ – የካርዲዮ ወይም የኤሮቢክ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ፥ ለአዕምሮ እና አካላዊ ጤንነት ፍቱን ነው ይላሉ የዘርፉ ባለሙያዎች፡፡

አላስፈላጊ ውፍረትን በመቀነስም ሆነ ሳይመጣ ለመከላከል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አይነት መስራት አስፈላጊ መሆኑንም ነው ባለሙያዎቹ የሚናገሩት፡፡

በዚህም በሣምንት እስከ 150 ደቂቃ በመስራት የአካልና የአዕምሮን ጤና እንዲጠብቁ ይመከራል ሲል የዘገበው ኸልዝላይን ነው፡፡

ሌላው ከሠዎች ጋር ያለን ማህበራዊ ግንኙነት በትኩረት መመልከት እንደሚያስፈልግም ነው ባለሙያዎቹ የሚመክሩት።

ከጓደኞችዎ ፣ ከቤተሰብና ጎረቤት እንዲሁም ሌሎች ሰዎች ጋር የየዕለት ግንኙነትዎን ማሻሻልና መልካም ማድረግ ለአዕምሮ ሰላምና ጤንነት አስፈላጊ ነው ይላሉ ጥናቶች፡፡

ጥልቅ ተመስጦ (ሜዲቴት) – ለጭንቀትና ተያያዥ ችግሮች መፍትሄ ነው ይባልለታል፡፡

‘’ሜዲቴት’’ የሚያደርጉ ሰዎች ህይወታቸውን ቀለል በማድረግ ከጭንቅት፣ ከበሽታ እና ከተለያዩ አዕምሯዊ ችግሮች ራሳቸውን ነጻ በማድረግ ጤናማ ህይወት እንደሚመሩ ይነገራል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.