Fana: At a Speed of Life!

በተለያዩ ዘርፎች ስልጠና በመስጠት በርካታ ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ እድሎች ተፈጥረዋል – የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ ጥር 17 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ስድስት ወራት ለዜጎች አስፈላጊውን ስልጠና በመስጠት በተለያዩ ዘርፎች በርካታ ቋሚ እና ጊዜያዊ የሥራ እድሎች መፍጠር መቻሉን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
 
ሚኒስቴሩ ከክልሎችና ተጠሪ ተቋማቱ ጋር የ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት አፈፃፀም እየገመገመ ነው፡፡
 
በመድረኩ ባለፉት ስድስት ወራት የዜጎችን ክህሎት ማዳበር የሚያስችሉ የተለያዩ ስልጠናዎች መሰጠታቸው ተመላክቷል፡፡
 
በተለይም በስራ እድል ፈጠራ እንዲሁም በቴክኒክ እና ሙያ ነባራዊ ሁኔታውን ያገናዘቡ ስልጠናዎች እንደተሰጡ መገለጹንየሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቦዘነች ነጋሽ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮፖሬት ተናግረዋል፡፡
 
የስልጠናውን ጥራት እና ተደራሽነት በሁሉም ክልሎች በተመጣጣኝ መልኩ ለማሳደግም በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን ጠቁመዋል፡፡
 
ሚኒስቴሩ አዲስ እሳቤ ከግምት ያስገባ ዕቅድ እንዲታቀድ እና ይህንን ታሳቢ ያደረገ ስራ እንዲሰራ ለማስቻልም ከ5 ሺህ በላይ ለዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱም ነው የተገለጸው፡፡
 
በዚህም ባለፉት ስድስት ወራት በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች 1 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ ለሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩ ተመላክቷል፡፡
 
በመላኩ ገድፍ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.