ባሕር ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ድርጅት በ6 ወራት 19 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ገቢ አገኘ
አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በሥድስት ወራት 19 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።
ድርጅቱ የበጀት ዓመቱን የሥድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሮባ መገርሳ ÷ ባለፉት ሥድስት ወራት ድርጅቱ የ2 ነጥብ 4 ሚሊየን ቶን የኦፕሬሽን አገልግሎት መስጠቱን ገልጸዋል።
አቶ ሮባ ፥ ድርጅቱ 312 ሺህ ቶን ብትን እንዲሁም 4 ሺ 500 በኮንቴይነር የታሸገ ጭነት ማጓጓዙንም ነው የተናገሩ።
በኮንቴይነር ከተጓጓዙት ጭነቶች መካከል 3 ሺህ 79 ያህሉ በሀገር ውስጥ መታሸጋቸውን እንደጠቆሙም ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በአጠቃላይ ኢ.ባ.ት.ሎ.ድ ከላይ የተጠቀሱትን አገልግሎቶች ባለፉት ሥድስት ወራት አቅርቦ 19 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱም ነው የተመለከተው፡፡