Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 17 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ በተለያዩ ዘርፎች በትብብር እና በቅንጅት መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ለይ መክረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሁለቱ ሀገራት 125 ዓመታትን ያስቆጠረ በመተማመን እና በመከባበር ላይ የተመሰረተ ግንኙነት እንዳላቸውም አውስተዋል፡፡

ከወዳጄ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በሚኖረኝ ውይይት ሁል ጊዜም ደስተኛ ነኝ ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.