Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ግብርናን በማዘመን በምግብ ራስን ለመቻል የምታደርገው ጥረት ለአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ ይሆናል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ግብርናን በማዘመን በምግብ ራስን ለመቻል እያደረገች ያለው ጥረት ለአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ እንደሚሆን ተገለጸ።

“አፍሪካን እንመግብ” በሚል መሪ ሐሳብ የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ብሎም ራስን መቻል ላይ ያተኮረ ስብሰባ በሴኔጋል ዳካር እየተካሔደ ነው፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ በስብሰባው ላይ በፈረንጆቹ ከ2016 እስከ 2022 ተግባራዊ የተደረገውን የመጀመሪያውን ሀገራዊ የምግብና ግብርና አቅርቦት ኮምፋክ የተሰኘው ፕሮግራም ያመጣውን ለውጥ አቅርበዋል፡፡

አጠቃላይ ግብርናውን በተመለከተ ኢትዮጵያ እያደረገቻቸው የሚገኙ ጥረቶችን በተመለከተ ለተለያዩ ሀገራት መሪዎች እና የልማት አጋር ድርጅቶች ገለጻ አድርገዋል።

በተጨማሪም የአፍሪካ ልማት ባንክ በመጀመሪያ የፕሮግራሙ ትግበራ ወቅት ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራስን ለመቻል የሄደችበት መንገድና ያሳካችው ውጤት እንደምሳሌ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በቀጣይም ከ2023 እስከ 2027 ለአምስት ዓመታት ተግባራዊ የሚደረግ ሁለተኛ ዙር ሀገራዊ የምግብና ግብርና አቅርቦት ኮምፋክ የተሰኘ ፕሮግራም መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያም በሁለተኛው የፕሮግራም ትግበራ ወቅት የስንዴ ምርት ሙሉ በሙሉ የሀገር ውስጥን ፍላጎት ከማሟላት አልፎ ወደ ውጪ ለመላክ፣ ለምግብ ዘይት ግብዓት የሚሆን አኩሪ አተር በብዛት ለማምረት እና የዶሮ ስጋና እንቁላል አቅርቦት በማሳደግ ላይ ትኩረት አድርጋ ለመስራት ዕቅድ እንደያዘች ተመላክቷል።

ዕቅዱን ተግባራዊ ለማድረግም 2 ነጥብ 84 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚያስፈልግ እና የሚሸፈነውም ከመንግስት በጀት፣ በግሉ ዘርፍ ተሳትፎ እና ከልማት አጋር አካላት ከሚገኝ ድጋፍ ነው መባሉን የፕላንና ልማት ሚኒስትር መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.