Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያውያን እና ጃማይካውያን አርቲስቶች የተጣመሩበት የሙዚቃ ድግስ በጃማይካ ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “ዘሮያል ፌስት” የተሠኘ ኢትዮጵያውያን እና ጃማይካውያን አርቲስቶች የተጣመሩበት የሙዚቃ ዝግጅት በጃማይካ ሞንቲጎ ቤይ ሊካሄድ ነው።

ኢትዮጵያን ይበልጥ ለዓለም ለማስተዋወቅ እና ዓለምአቀፍ ጎብኚዎች እንዲጎበኟት ለማነሳሳት ያለመ ዝግጅት መሆኑ ተገልጿል፡፡

ዝግጅቱን ያሠናዱት “አቢሲንያ ኢንተርቴይመንት” እና “ንጉሥ ኢንተርቴይመንት” መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

የሙዚቃው ድግስ ከግንቦት 18 እስከ 20 ቀን 2015 ለሁለት ቀናት በጃማይካ ሞንቲጎ ቤይ ይቆያል፡፡

በዝግጅቱ ላይ ድምፃዊ ዳዊት ጽጌ፣ ሳሚ ዳን፣ ልጅ ሚካኤል፣ ካስማሰ፣ ዩሐና፣ ኒና ግርማ እና ያሬድ ነጉ ደግሞ ከኢትዮጵያ የሙዚቃ ሥራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ ተገልጿል፡፡

ከጃማይካ የሬጌ ሙዚቃ አቀንቃኞች ጄሲ ሮያል፣ ሲዝላ ኮሎንጂ፣ ጅሶን ፓንቶን፣ ሚኪ ግንራል የሙዚቃ ሥራቸውን እንደሚያቀርቡ ተጠቁሟል፡፡

አሰናጂዎቹ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ በዝግጅቱ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን አዘጋጆቹን በማነጋገር መሳተፍ ይችላሉ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.