Fana: At a Speed of Life!

ጃክ ማ ሁለተኛ ዙር የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ቁሳቁሶችን ለአፍሪካ ሀገራት ላኩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሊባባ ፋውንዴሽን መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ ጃክ ማ ሁለተኛ ዙር የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ቁሳቁሶችን ለአፍሪካ ሀገራት መላካቸውን አስታወቁ።

የጃክ ማ ፋውንዴሽን ከዚህ ቀደም የአፍሪካ ሃገራት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያደርጉትን ጥረት ለማገዝ የሚውል የቁሳቁስ ድጋፍ መላኩ ይታወሳል።

ቻይናዊው ቢሊየነር ለአፍሪካ ሀገራት የሚያደርጉትን ድጋፍ በመቀጠል ለአፍሪካ ሃገራት የሚሰራጩ የህክምና መርጃ ቁሳቁሶች መንገድ ላይ እንደሚገኙ በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል።

ሁለተኛው ዙር ድጋፍ 500 የመተንፈሻ መሳሪያዎች ( ቬንትሌተር)፣ 200 ሺህ የፊት መሸፈኛዎችና የህክምና ሙሉ ልብሶች፣1 ሚሊየን ናሙና መውሰጃ ፣ 2 ሺህ የሰውነት ሙቀት መለኪያ እና 500 ሺህ ጓንቶች ለአፍሪካ ሀገራት መላካቸውን ገልፀዋል።

ጃክ ማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቁሳቁሶቹ ለአፍሪካ ሀገራት እንዲደርሱ እያደረጉት ላለው ትብብር ምስጋና አቅርበዋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.