Fana: At a Speed of Life!

የመጀመሪያው የዳያስፖራ አደረጃጀቶች የእውቅና መርሐ ግብር ዛሬ ይካሔዳል

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመጀመሪያው የዳያስፖራ አደረጃጀቶች የእውቅና መርሐ ግብር ዛሬ እንደሚካሔድ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በሀገር ውስጥ በሚገኙ የዳያስፖራ ማኅበራት÷ ለመጀመሪያው የዳያስፖራ አደረጃጀቶች የእውቅና መርሐ ግብር ወደ ሀገር ቤት ለመጡ አመራሮችና ተወካዮች ትናንት የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ተደርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር መሐመድ እንድሪስ የዳያስፖራ አደረጃጀት አመራሮቹ አባላቶቻቸውን አስተባብረው ላከናወኗቸው ተግባራት አመስግነዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካይና በሀገር ውስጥ የሚገኙ የዳያስፖራ ማኅበራት አመራሮችም የዳያስፖራ አደረጃጀት መሪዎቹ የሚኖራቸው ቆይታ የተሳካ እንዲሆን አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የዳያስፖራ አደረጃጀት መሪዎቹ በበኩላቸው ስለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነው÷ ዳያስፖራውን በማስተባበር በሀገራዊ ልማት ውስጥ ያለውን ሚና ይበልጥ ለማሳደግ እንሠራለን ብለዋል፡፡

በቀጣይ የሚኖረው የዳያስፖራ ተሳትፎ በሚመራባቸው መሰረታዊ መርሆዎች ላይ ውይይት ተደርጎ መግባባት ላይ መደረሱን ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.