Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ከተመድ የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ከተመድ የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅት ረዳት ዋና ፀሀፊ ጋር እና በኢትዮጵያ የተመድ ሰብዓዊ እርዳታ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ፅህፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር ሁሴን ሃሺን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀኃፊ የሀገር ውስጥ ስደት ጉዳዮች ልዩ አማካሪ ሮበርት ፓይፐርና በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት  የሰብዓዊ እርዳታ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር ካትሪን ሶዚ ጋር መክረዋል፡፡

ልዑኩ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና ከሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በክልሉ የሰብዓዊ እርዳታ ዙሪያ እንደሚመክር ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.