Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ መድረክ በደብረ ማርቆስ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ መድረክ በደብረ ማርቆስ ከተማ ተካሄደ፡፡

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ናሰፈሩት ጽሑፍ፥ በዘርፉ እየተመዘገበ ያለው ውጤት ተስፋ ሰጪ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የአምራች ኢንዱስትሪዎች ዕድገትና መስፋፋት ለሀገራዊ ብልፅግናችን የማይተካ ሚና አለው ብለዋል፡፡

ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ማስመዝገብ የሚቻለውም ሁሉን አቀፍ ልማት በማረጋገጥ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

በመሆኑም አምራች ዘርፉ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር የሚችልና ለኢኮኖሚያችን ዕድገት እውን መሆን ወሳኝ ነው ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡

በዚህም በዘርፉ ለተሰማሩ ባለሃብቶች የምናደርገውን ድጋፍ አጠናክረን እንቀጥላለን ነው ያሉት፡፡

በደብረ ማርቆስ ከተማ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርቶች መጎብኘታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.