Fana: At a Speed of Life!

ፈረንሳይ ወታደሮቿን ከቡርኪና ፋሶ ለማስወጣት ተስማማች

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፈረንሳይ ወታደሮቿን ከቡርኪና ፋሶ ለማስወጣት መስማማቷን ገለፀች።

የአሁኑ የፈረንሳይ መንግስት ወታደሮቸን አስወጣለሁ መግለጫ ቡርኪናፋሶ የፈረንሳይ ወታደሮች ሀገሬን ለቀው ይውጡ በማለት ያቀረበችውን ጥያቄ ተከትሎ የመጣ ነው ተብሏል።

የቡርኪና ፋሶ መንግስት የ2018ቱን ወታደራዊ ስምምነት በይፋ ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ የፈረንሳይ መንግስት ወታደሮቹ ከቡርኪና ፋሶ እንደሚወጡ በትናንትናው ዕለት አስታውቋል፡፡

የፈረንሳይ ልዩ ኃይል የቀድሞ ቅኝ ግዛቷ በነበረችው ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ቡርኪና ፋሶ የተሰማራው በሀገሪቱ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ተልዕኮ በሚል እነደነበር አር ቲ በዘገባው አስታውሷል።

የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በ30 ቀናት ውስጥ ወታደሮቹ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የሚያዘውን ማስጠንቀቂያ ከኦጋዱጉ ማክሰኞ ዕለት መቀበሉን ገልጿል።

ትዕዛዙን ተከትሎ መግለጫ የሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኩዋይ ዲ ኦርሴይ÷ የስምምነቱን ውሎች እና ጥያቄውን እናከብራለን ሲሉ ተናግረዋል።

እንደ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገባ÷ ወታደሮቹ በየካቲት ወር መጨረሻ ላይ ቡርኪናፋሶን ለቀው ይወጣሉ።

እስከ ሚያዝያ ወር መጨረሻ ድረስም መሳሪያዎቻቸውን ጠቅልለው እንደሚወጡም ተጠቁሟል።

በቡርኪና ፋሶ 400 ያክል ወታደሮች እንደሚገኙ ዘገባው ያመላክታል።

ከወራት በፊት የቡርኪና ጎረቤት የሆነችው ማሊ የፈረንሳይ ወታደሮች ሀገሯን ለቀው እንዲወጡ ማድረጓ የሚታወስ ነው።

በወቅቱ ፈረንሳይ ማሊን ለዚህ ያነሳሳቻት ሩሲያ ናት በሚል ወቀሳ ማቅረቧም ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.