Fana: At a Speed of Life!

36ኛው የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ የአፍሪካ ሀገራት የነፃ ገበያ ትግበራ ማፋጠን ላይ ትኩረቱን ያደርጋል ተባለ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የአፍሪካ ሀገራት የነፃ ገበያ ትግበራ ማፋጠን ላይ ትኩረቱን እንደሚያደርግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉባኤውን ለማካሄድ የተደረጉ ዝግጅቶችን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

የአፍሪካ ሀገራትን የንግድና ትስስር ማሳደግን ትኩረት ያደረገው ጉባኤው በፈረንጆቹ ከየካቲት15 እስከ 19 ቀን ድረስ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

የሚኒስትሮች ስብሰባው ከመሪዎቹ ጉባኤ ሁለት ቀናት ቀደም ብሎ የካቲት15 የሚካሄድ ሲሆን ከየካቲት 18 እስከ 19 ደግሞ የመሪዎቹ ጉባኤ ይደረጋል።

ጉባኤውን በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ 30 ተቋማትን በአባልነት የያዘ ብሄራዊ የዝግጅት ኮሚቴ ተቋቁሞ ስራዎች በማከናወን ላይ ይገኛል ተብሏል።

በብሄራዊ ኮሚቴው የተሰሩ ስራዎችን በተመለከተ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በትናንትው እለት ሪፖርት ቀርቦ ግምገማ እንደተደረገበት የሚታወስ ነው።

በትዕግስት ብርሃኔ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.