Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት ስምንት ወራት ከወጪ ንግድ 1 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር ተገኘ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በበጀት ዓመቱ ስምንት ወራት ከወጪ ንግድ 1 ነጥብ8 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር መገኘቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ በስምንት ወራቱ 2 ነጥብ 3 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅዶ 1 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር ወይም የእቅዱን 79 በመቶ ማሳከቱን አስታውቋል።

ይህ አፈፃፀም ከአምናው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወራት ከተገኘው 1 ነጥብ 6 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ጋር ሲነፃፀር በ171 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ጭማሪ ማሳየቱ ተገልጿል።

የሚኒስቴሩ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወንድሙ ፍላቴ፥ አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ጫት ከተያዘላቸው ዕቅድ በላይ አፈጻጸም ያስመዘገቡት የወጪ ንግድ ምርቶች መሆናቸውን ገልጸዋል።

እንዲሁም የዕቅዳቸውን ከ50 በመቶ እስከ 90 በመቶ ክንውን ያስመዘገቡ የወጪ ምርቶች ደግሞ ቡና፣ የቅባት እህሎች፣ ስጋ፣ ጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ የጥራጥሬ ሰብሎች እና የቅመማ ቅመም ምርቶች ናቸው ብለዋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.