Fana: At a Speed of Life!

የዓለም አቀፍ የትምህርት አጋርነት ድርጅት በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፉን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፍ የትምህርት አጋርነት ድርጅት በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፉን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከዓለም አቀፍ የትምህርት አጋርነት ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ ላውራ ፍረጀንት ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም ፕሮፌሰር ብርሃኑ÷በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተደረጉ ለውጦችን እና እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን በሚመለከት ገለጻ አድርገዋል፡፡

የትምህርት ጥራትንና ፍትሀዊነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።

የዓለም አቀፍ የትምህርት አጋርነት በኢትዮጵያ በትምህርት መስክ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ጠቅሰው÷ አሁንም ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

ላውራ ፍረጀንት በበኩላቸው÷በኢትዮጵያ በትምህርት ተደራሽነትና መስፋፋት የተከናወኑ ተግባራት አመርቂ ውጤት እየተገኘባቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ድርጅታቸውም በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፉን ለመደገፍ ከዓለም አቀፍ ለጋሾች ጋር በመወያየት ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በኢትዮጵያ በትምህርት መስክ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ የኢትዮጵያ መንግስት እያደረገው ያለውን ተግባርም ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አድንቀዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.