Fana: At a Speed of Life!

ከ420 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የከረጢት ፋብሪካ ሥራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ ከ420 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በደብረ ማርቆስ ከተማ የተገነባውን የከረጢት ፋብሪካ መርቀው ሥራ አስጀመሩ።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱም የፌደራል፣የክልል፣የከተማ አስተዳደር የስራ ሃላፊዎችና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

ፋብሪካው በአሁኑ ሰዓት ለ350 ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠሩን ከደብረ ማርቆስ ከተማ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ፋብሪካው በጋዜል ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መገንባቱ ታውቋል፡፡

እንዲሁም ርዕሰ መስተዳድሩ በደብረ ማርቆስ ከተማ በአምራች ኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፍ ከተሰማሩ አልሚዎች ጋር ዛሬ ተወያይተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.