Fana: At a Speed of Life!

የጌዴኦ ብሄረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጌዴኦ ብሄረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል “ደራሮ ለዘላቂ ሰላም እና ልማት” በሚል መሪ ቃል በጌዲኦ ዞን ዲላ ከተማ ዋዜማው በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ነው፡፡

በተለይ በቡና፣ በፍራፍሬ እንዲሁም በእንሰት ምርቱ የሚታወቀው ዞኑ በዋዜማው በከተማው አደባባይ 20 ሺህ የቡና መጠጫ ሲኒ በረከቦት ላይ ዘርግቶ “ቡና ጠጡልኝ” ብሏል።

በዚህ ባህላዊ የደራሮ ቡና መጠጣት መሰናዶ ላይ የዞኑና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በቋንቋ ሲምፕዚየም፣በታሪካዊ ሥፍራዎች ጉብኝት እንዲሁም በተለያዩ የአደባባይ ክብረ በዓላት ትርዒት የደመቀው የጌዲዮ ብሄረሰብ “ደራሮ” የዘመን መለወጫ በዓል በነገው ዕለት ይከበራል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.