Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ባላይ የሚያወጣ ሲጋራ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ ሲጋራ መያዙ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ሲጋራው ከድሬዳዋ በአይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ ተጭኖ ወደ ሀረር ከተማ ሊገባ ሲል ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ ደንገጎ የፍተሻ ኬላ ላይ በሐረማያ ወረዳ ፖሊስ መያዙን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ዲቪዥን ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ቶሎሳ ጎሹ ተናግረዋል፡፡

የተያዘው 100 ካርቶን ሲጋራ በህገ ወጥ መንገድ ድንበር አቋርጦ ወደ ከተሞች በማስገባት ሊሰራጭ እንደነበር ዋና ኢንስፔክተር ቶሎሳ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

የተሽከርካሪው ሠሌዳ ቁጥርና ቦሎው ላይ ያለው ቁጥር የተለያየ መሆኑን የገለጹት ዋና ኢንስፔክተሩ ÷አሽከርካሪው ለጊዜው ከአባቢው መሰወሩንና በፖሊስ ክትትል እየደረገበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የተያዘው ሲጋራ ከነተሸከርካሪው ሀረር ደከር የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ገቢ መደረጉንም ጠቁመዋል፡፡

በተሾመ ኃይሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.