Fana: At a Speed of Life!

ካፍ ለቻን ውድድር አሸናፊ የሚሰጠውን የገንዘብ ሽልማት አሳደገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአልጀሪያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው የቻን ውድድር አሸናፊ ለሚሆነው ሀገር የሚሰጠውን የገንዘብ ሽልማት መጠን ማሳደጉን የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

የአፍሪካ እግርኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሙትሴፔ እንደገለፁት ፌደሬሽኑ ለቻን አሸናፊ ሀገር የሚሰጠውን የገንዘብ ሽልማት 60 በመቶ መጨመሩን ገልጸዋል፡፡

ውሳኔው በአፍሪካ አህጉር ውስጥ የሚደረጉ ውድድሮች ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጣቸው ለማድረግ ያለመ መሆኑንም ነው ፕሬዚዳንቱ የተናገሩት፡፡

በዚህም በአልጀሪያ ኔልሰን ማንዴላ ስታዲየም በሚደረገው የፍፃሜ ጨዋታ አሸናፊ ለሚሆነው ሀገር የ2 ሚሊየን ዶላር ሽልማት እንደሚሰጠው አመላክተዋል፡፡

ይሀም ከዚህ ቀደም አሸናፊ የሆነ ሀገር ያገኝ ከነበረው የ1 ሚሊየን 250 ሺህ ዶላር ሽልማት አንጻር ከፍ ያለ መሆኑ ነው የተገለጸው።

ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ለሚያጠናቅቅ ሀገር 800 ሺህ እንዲሁም 3ኛ እና 4ኛ በመሆን ለሚያጠናቅቁ ሀገራት ለእያንዳንዳቸው የ500 ሺህ ብር ሽልማት እንደሚበረከትላቸው ተናግረዋል፡፡

የአፍሪካ ሀገራት የቻን ውድድር በፈረንጆቹ የካቲት 4 እንደሚጠናቀቅ ካፍ ኦንላይን ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.