Fana: At a Speed of Life!

በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት በማምጣት ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበው ተማሪ ሚኪያስ አዳነ

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ተማሪ ሚኪያስ አዳነ በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈታና ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት በማምጣት ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል፡፡

የደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ተማሪዎች ተማሪ ሚኪያስ አዳነ ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት በማምጣት በሀገር አቀፍ አንደኛ መሆኑን የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ገልጸዋል፡፡

የኮቪድ-19 እና የነበረው ግጭት ተፅዕኖ ባይኖር ከዚህ በላይ ነጥብ ማስመዝገብ ይቻል ነበር ብለዋል።

በቀጣይም ከዚህ የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ እንዳነሳሳቸው ተናግረዋል፡፡

ትምህርት ቤቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ካስፈተናቸው 69 ተማሪዎች እስካሁን ውጤታቸው ከታየላቸው 47 መካከል÷ ከ21 በላይ የሚሆኑት ከ600 በላይ፣ 25ቱ ከ500 እስከ 599 እና1 ተማሪ 478 ነጥብ አስመዝግበዋል፡፡

እንዲሁም ከተፈተኑት 15 ሴት ተማሪዎች እስካሁን ውጤታቸው ከታየላቸው መካከል 5ቱ ከ600 እስከ 635 ነጥብ ማምጣታቸውን የደሴ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.