Fana: At a Speed of Life!

በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ 141 ተጋላጭ ፍልሰተኞችን መታደጉን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 19 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከጅቡቲ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ጋር በመተባበር  141 ተጋላጭ ፍልሰተኞችን መታደጉን አስታወቀ።

ፍልሰተኞቹ አደገኛ በሆነ ሁኔታ በህገ ወጥ ሰው አዘዋዋሪ ጀልባ ወደ የመን ይጓዙ እንደነበርም ኤምባሲው አስታውቋል።

በቀይ ባህር የጅቡቲዋ ጎዶሪያ ጠረፋማ የባህር ክልል ፍልሰተኞቹን መታደግ መቻሉንም ገልጿል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ ሁለት ግለሰቦች በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ተከሰው በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ነው የገለጸው።

ኤምባሲው በትናንትናው እለት በጅቡቲ ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ቢሮ ጋር በመተባበር 160 ተጋላጭ ፍለሰተኞችን ወደ ሀገራቸው መመለሱ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.