Fana: At a Speed of Life!

የአፋር ክልል መስኅቦችን ለማስተዋወቅ ያለመ ጉብኝት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል የሚገኙ የመስኅብ ሥፍራዎችን ለማስተዋወቅ ያለመ የጉብኝት መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።

መርሐ ግብሩ ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ቀናት የሚቆይ መሆኑ ተገልጿል።

የጉብኝት መዳረሻዎቹም፥ ኤርታሌ፣ ዳሎል፣ ዓሣአሌ የጨው ኃይቅ እና የጨው ንጣፍ አካባቢዎች መሆናቸው ተመላክቷል።

ከአሜሪካ፣ ጅቡቲ፣ አዲስ አበባ፣ ሐዋሳ እና ከአፋር ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ የሕብረተሰብ ክፍሎች በጉብኝቱ እየተሳተፉ ነው።

የጉብኝቱ ዓላማ የመስኅብ ሥፍራዎችን በማስተዋወቅ የቱሪዝም እንቅስቃሴውን ማነቃቃትና ማሳደግ መሆኑን የጉብኝቱ አስተባባሪ ያሲን ከድር ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

ጉብኝቱ በነፃ መሆኑንና የጎብኚዎቹ ቁጥርም ከ150 እስከ 200 እንደሚገመትም ነው የተናገሩት።

በአፋር በርካታ መስኅብ መኖሩን ጠቅሰው በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኙ ሰዎች ክልሉን እንዲጎበኙ ጥሪ አቅርበዋል።

በዮሐንስ ደርበው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.