Fana: At a Speed of Life!

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ማኅበር 10 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ተረከበ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 20 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው እለት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የቅዱስ ጊዩርጊስ የስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ማህበር 10 ሺህ ካሬ ሜትር የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታ ርክክብ አድርገዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች ከቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ጋር ውይይት ባካሄዱበት ወቅት ደጋፊዎቹ ካነሷቸው በርካታ ጥያቄዎች መካከል አንደኛው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን የማስፋፋት ጥያቄ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ማህበር የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ በቦታው ላይ የነበሩ የተለያዩ ህገወጥ ደላሎችንና የይገባኛል ጥያቄዎችን በመፍታት ለክለቡ ደጋፊዎች ማህበር በቦታው በመገኘት ማስረከባቸው ተገልጿል፡፡

ከንቲባ አዳነች በዚሁ ጊዜ በከተማው የተለያዩ የልማት ስራዎቻችን ከህገወጥ ደላሎች ጋር ትንቅንቅ በማድረግ የልማት እቅፋቶችን እየተጋፈጥን በርካታ ስራዎችን እየሰራን ነው ብለዋል

በመሆኑም ህብረተሰቡ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በየአካባቢው ለልማት እንቅፋት የሚሆኑ ህገወጥ እቅስቃሴዎችን በመግታት ሚናውን እንዲወጣ ጥሪ ማቅረባቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ዛሬ ርክክብ የተደረገበት ቦታም በፍጥነት ወደ ልማት እንዲገባ አቅጣጫ የሰጡ ሲሆን፥ የክለቡ ቦርድም በፍጥነት ግንባታውን እንደሚያስጀምር ቃል ገብቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.