Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ብሪታንያ የ965 ሚሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያና ብሪታንያ መካከል የ965 ሚሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈረመ።

ስምምነቱን የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አድማሱ ነበበ እና በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት ተወካይ ክርስቲያን ሮግ ተፈራርመውታል።

ድጋፉ በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞችን እና ስደተኞች በሚገኙባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑ ነው የተነገረው።

በዚህም ትምህርት፣ ጤና እና መጠለያን ጨምሮ የተለያዩ መሰረታዊ ፍላጎቶችን ማሟላት የሚያስችሉ ስራዎች የሚሰሩ ይሆናል።

ዋና ትኩረቱንም የስደተኞችን እና የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚነት ማረጋገጥና አዲስ የሚገቡ ስደተኞችን ማስተናገድ የሚያስችል አቅምን መፍጠር ነው ተብሏል።

በዚህም 200 ሺህ ስደተኞችና የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ያደርጋል መባሉን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.