Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች የአፍሪካን የግብርና ምርቶች ለማሳደግ የ30 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ቃል ገቡ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 20 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፍ የልማት አጋር ድርጅቶች ለአፍሪካ አህጉር የግብርና ምርቶችን ለማሳደግ የሚውል የ30 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡

ዓለም አቀፍ የልማት አጋር ድርጅቶች የተሳተፉበት እና በሴኔጋል ዳካር የተካሄደው 2ኛው የአፍሪካ የምግብ ጉባዔ በትናንትናው ዕለት መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

በጉባዔው መጠናቀቂያም የልማት አጋሮች የአፍሪካን የግብርና ምርት በማሳደግ አፍሪካ “የዓለም አቀፍ የዳቦ ቅርጫት” እንድትሆን በቅንጅት እንሰራለን ብለዋል ፡፡

ለዕቅዱ ተግባራዊነትም ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች ለአፍሪካ የ30 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባታቸው ነው የተገለጸው፡፡

ከዚህም ውስጥ የአፍሪካ ልማት ባንክ 10 ቢሊየኑን በ5 ዓመታት ውስጥ ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል የገባ ሲሆን÷ እስላማዊ ልማት ባንክ በበኩሉ 5 ቢሊየን ዶላር ያህሉን ለመስጠት ቃል ገብቷል፡፡

በሴኔጋል መንግስት እና በአፍሪካ ልማት ባንክ በተዘጋጀው የዳካሩ ጉባዔ 34 የሀገራት መሪዎች፣ የ70 ሀገራት ሚኒስትሮች እና የልማት አጋሮች የአህጉሪቱን የግብርና ምርቶች ለማሳደግ የመከሩበት እንደነበር መገለጹን የአፍሪካ ልማት ባንክ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.