Fana: At a Speed of Life!

በጀርመን በተካሄደ የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቶች አሸነፉ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 20 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጀርመን ካርልስሩህ በተካሄደ የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቶች በ3 ሺህ ሜትር በሁለቱም ጾታዎች ድል ቀንቷቸዋል፡፡

በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ አምስት ተከታትለው በመግባት ውድድሩን በበላይነት አጠናቀዋል፡፡

አትሌት ለምለም ኃይሉ 8 ደቂቃ ከ37 ሰከንድ ከ55 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ነው ውድድሩን በአንደኝነት ያሸነፈችው።

አትሌት ወርቁውሃ ጌታቸው 8 ደቂቃ ከ37 ሰከንድ ከ98 ማይክሮ ሰከንድ ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት ዳዊት ስዩም 8 ደቂቃ ከ39 ሰከንድ ከ20 ማይክሮ ሰከንድ ሶስተኛ ወጥተዋል።

አትሌት ሚዛን ዓለም እና አትሌት ዘርፌ ወንድማገኝ አራተኛና አምስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

በወንዶች 3 ሺህ ሜትር አትሌት አብዲሳ ፈይሳ በ7 ደቂቃ ከ40 ሰከንድ ከ35 ማይክሮ ሰከንድ አሸናፊ ሲሆን÷ በርቀቱም የቦታውን ክብረ ወሰን ማሻሻሉ ተገልጿል፡፡

ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት አዲሱ ግርማ 7 ደቂቃ ከ41 ሰከንድ ከ53 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ሶስተኛ ደረጃ መያዙን የወርልድ አትሌቲክስ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.