Fana: At a Speed of Life!

የቃጠሎ አደጋ የደረሰበትን የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ጽ/ቤት ህንፃ በተሻለ ሁኔታ ለመስራት ርብርብ እየተደረገ ነው- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቃጠሎ አደጋ የደረሰበትን የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ጽህፈት ቤት ህንፃ በአጭር ቀን ውስጥ መልሶ በተሻለ ሁኔታ ለመስራት ርብርብ እየተደረገ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።

ቃጠሎ የደረሰበት ሕንፃ በውስጡ የነበሩ የህብረተሰቡም ሆነ የመንግስት ምንም አይነት ሰነዶች ለእሳት አለመዳረጋቸውን ለማረጋገጥ እንደተቻለም ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ90 ቀናት ውስጥ ለመፈፀም የታቀዱ ስራዎችም በአስደናቂ ፍጥነትና ጥራት እየተከናወኑ እንደሚገኙም ጠቁመዋል፡፡

በተለይም ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች የሚገነቡት 240 ቤቶችን የያዙ ባለ 5 ወለል 6 ህንፃዎች እና አረንጓዴ ስፍራዎች ማራኪና አካባቢውን መለወጥ በሚያስችል ሁኔታ እየተሰሩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

የሌማት ትሩፋት፣ የዳቦና የምገባ ግንባታዎች በመጠናቀቅ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ማየት መቻሉንም ጠቅሰዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.