Fana: At a Speed of Life!

በወምበርማ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ5 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ጎጃም ዞን ወምበርማ ወረዳ ጎመር ቀበሌ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአምስት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

አደጋው የደረሰው  ዛሬ ጠዋት ገልባጭ ሲኖ ትራክ መኪና ከዓባይ በረሃ አካባቢ አሸዋ ጭኖ ሲመለስ ዳገት ላይ በመገልበጡ  ምክንያት መሆኑን የምዕራብ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

በመመሪያው የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ክፍል ሃላፊ ኮማንደር አበበ አጥቆ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷በአደጋው አሸዋ በጫነው ሲኖ ትራክ መኪና ላይ ተሳፍረው የነበሩ አምስት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ አልፏል፡፡

በተጨማሪም በአደጋው ሁለት ሰዎች ላይ  ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ነው ኮማንደር አበበ የተናገሩት፡፡

ኮማንደር አበበ በአካባቢው አሸዋ  እና እንጨት የሚጭኑ አሽከርካሪዎች ሰራተኞችን እና ሌሎች ሰዎችን ከላይ የማሳፈር ተገቢ ያልሆነ ልምድ መኖሩን  ጠቁመዋል፡፡

ስለሆነም ማህበረሰቡም ሆነ አሽከርካሪዎች ከመሰል  ህገ ወጥ ድርጊት ራሳቸውን ሊቆጥቡ እንደሚገባ  አሳስበዋል፡፡

 

በመላኩ ገደፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.