Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ኮሪያ÷አሜሪካ ለዩክሬን የጦር ታንክ እሰጣለሁ ማለቷን አወገዘች

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ÷ አሜሪካ ለዩክሬን የሩሲያን ጦር ለመዋጋት የሚረዱ ዘመናዊ የጦር ታንኮችን ለማቅረብ የወሰደችውን ውሳኔ በጽኑ አወግዛለች፡፡

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን እህት ኪም ዮ ጆንግጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት አንዳሉት÷አሜሪካ በሩሲያ-ዩክሬን ግጭት ሩሲያን ለማዳከም እና ቀጠናውን ይበልጥ ለማተራመስ እየሰራች ነው፡፡

ዋሽንግተን “ቀይ መስመር” አልፋለች ያሉት ባለስልጣኗ÷ዩናይትድ ስቴትስ በቀጠናው ሞስኮን ለማዳከም ያለመ “የውክልና ጦርነት” እያካሄደች ነው ሲሉም ወንጅለዋል።

ኪም ዮ ጆንግ ፒዮንግያንግ በየትኛውም ጊዜ እና ሁኔታ ከሩሲያ ሕዝብ እና መንግስት ጎን እንደምትቆምም አረጋግጠዋል፡፡

አሜሪካ ለዩክሬን አውዳሚ የጦር መሣሪያዎችን በማቅረብ ጦርነቱ እንዲባባስ የምታደርገው ጥረት በእጅጉ አሳሳቢ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ ጎን ለጎን ሰሜን ኮሪያ ከአሜሪካ እና የእስያ አጋሮቿ ጋር እያደገ የመጣውን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እና ሚሳኤል መርሐ ግብር መጋፈጧን እንደቀጠለች አርቲ በዘገባው አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.