Fana: At a Speed of Life!

የባቡር ሐዲድ ብረቶችን የሰረቁ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 20 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳማ ወረዳ መርማርሳ ቀበሌ የባቡር ሐዲድ ብረቶችን የሰረቁ አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
ተጠርጣሪዎቹ የባቡር ሐዲድ ብረቶችን በህገ-ወጥ መንገድ በመፍታት በኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አ.ማ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከፍተኛ ጫና መፍጠራቸው ተገልጿል፡፡
የክልሉ ፀጥታ አካላት ባደረጉት ከፍተኛ አሰሳ አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን÷ጉዳያቸው በህግ መታየት መጀመሩም ተጠቁሟል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ የዘረፏቸውን የባቡር ሐዲድ ብረቶች የሚደብቁበትን ቦታ እንዲያሳዩ በማድረግ ተጨማሪ የሐዲድ ብረቶች በሲኖ ትራክ ተጭነው መያዛቸውን ከአክሲዮን ማህበሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በአዳማ ወረዳ የመርማርሳ ቀበሌ ነዋሪዎች÷መሠል ችግሮች እንዳይከሰቱ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በቅርበት መስራታቸውን እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.