Fana: At a Speed of Life!

አራት የስኳር ፋብሪካዎች ወደ ምርት መመለሳቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አራት የስኳር ፋብሪካዎች ከታኅሣሥ እና ጥር ወር ጀምሮ ወደ ምርት መመለሳቸውን የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ አስታወቀ፡፡

እስካሁን ፊንጫ፣ ወንጂ ሸዋ፣ ኦሞ ኩራዝ 2 እና ኦሞ ኩራዝ 3 የስኳር ፋብሪካዎች የክረምት ወቅት አጠቃላይ ጥገና ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ ወደ ምርት መግባታቸውን በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የሕዝብ ግንኙነትና ተሳትፎ ዋና ክፍል ኃላፊ ረታ ደመቀ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም ጣና በለስ፣ ከሰም፣ አርጆ ዴዴሳ እና መተሐራ የስኳር ፋብሪካዎች ከጥር መጨረሻ እስከ መጋቢት ድረስ ወደ ምርት እንደሚገቡ አመላክተዋል፡፡

ያለውን የስኳር አቅርቦት እጥረት መሰረት በማድረግ ላለፉት ጥቂት ወራት ለሸማቾች የኮታቸውን 25 በመቶ ብቻ ይሰጣቸው እንደነበር አስታውሰው÷ ከጥር ወር ጀምሮ ግን የኮታቸውን 50 በመቶ ያገኛሉ ነው ያሉት።

ሁሉም ፋብሪካዎች ወደ ምርት ሲገቡ እና ከውጭ የሚገባውን ስኳር ጨምሮ የኮታቸውን መቶ በመቶ እንደሚያገኙም ጠቁመዋል፡፡

የስኳር ምርት አቅርቦቱን ለማሳደግ ከውጭ በግዥ ከሚገባው በተጨማሪ በሀገር ውስጥ የሚገኙ የስኳር አምራች ፋብሪካዎችን ወደ ምርት ማስገባት ትኩረት የተሰጠው ተግባር መሆኑንም አስረድተዋል።

በዮሐንስ ደርበው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.