Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ክልል ወጣቶች በብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ሊግ ውሳኔዎች ላይ እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የሐረሪ ክልል ወጣቶች በብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ሊግ ውሳኔዎች ላይ እየተወያዩ ነ ው፡ ፡

በብልፅግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽኅፈት ቤት የወጣቶች ሊግ “ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካ ብልፅግና የሚተጋ ወጣት” በሚል ርዕስ በቅርቡ በአዳማ በተካሄደው 1ኛ ጉባዔ ላይ መሣተፉ ይታወሳል፡፡

ሊጉ በተወሰኑ ውሳኔዎችና በተቀመጡ አቅጣጫዎች ላይ ከሐረሪ ክልል ወጣቶች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው፡፡

በጉባዔው ውሳኔዎች መሠረት ለወጣቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት መረጋገጥ ከማን ምን ይጠበቃል በሚል ርዕስ ውይይት እየተካሄደ ነው።

በብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ሊግ የመጀመሪያ ጉባዔ የተላለፉ ውሳኔዎች የሊጉ የሥራ አሥፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ለመድረኩ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።

የወጣቶች የመልካም አስተዳደር፣ የልማትና የሥራ ዕድል ፈጠራ ጥያቄዎች መልስ እንዲያገኙ ሊጉ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በስፋት እንቅስቃሴ መጀመሩም ተገልጿል።

አዳማ በተካሄደው የብልፅግና ፓርቲ የመጀመሪያው ጉባዔ ላይ ሥድስት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ውሳኔዎችን ማሳለፉ በወጣቶች የውይይት መድረክ ላይ ተነስቷል፡፡

ጠንካራ መዋቅር መገንባት በዚህም የወጣቱን ኢኮኖሚያዊ ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎን ማረጋገጥ፣ የኢትዮጵያን ሀገረ መንግስት የሚያጎለብቱ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትና ወንድማማችነት ላይ በማተኮር ከሀገር አልፎ አፍሪካዊ አቋም እንዲኖረው ማስቻል የሚሉት ፍሬ ነጥቦች ይገኙበታል ተብሏል።

በተሾመ ኃይሉ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.