Fana: At a Speed of Life!

በወቅታዊ ሀገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ከአርባ ምንጭ እና አካባቢዋ ነዋሪዎች ጋር ምክክር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በወቅታዊ ሀገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ከአርባ ምንጭ እና አካባቢዋ ነዋሪዎች ጋር የጋራ ምክክር በአርባምንጭ ከተማ መካሄድ ጀምሯል ።

የውይይት መድረኩን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽኅፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ ሚኒስትር አቶ አብርሃም አለኸኝ ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ ፣ የደቡብ ክልል የመንግስት ተጠሪ አቶ ጥላሁን ከበደ እና የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ እየመሩት መሆኑን ከጋሞ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በምክክር መድረኩ የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር እና ከአካባቢው የተውጣጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ይገኛል።

በተመሳሳይ በወላይታ ዞን በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ከኅብረተሰቡ ጋር እየተካሄደ ይገኛል፡፡

መድረኩን የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ሎሜ በዶ እየመሩት ነው፡፡

መድረኩ ከማን ምን ይጠበቃል በሚሉ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክርና ሁሉም የኅብረተሠብ ክፍል በቀጣይ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ለማከናወን አቅጣጫዎች እንደሚያስቀምጥም ተመላክቷል፡፡

በመድረኩ የፌደራል፣ የክልል፣ የዞንና የሶዶ ከተማ አመራሮች እንዲሁም ከሁሉም የኅብረተሰብ ማኅበራዊ መሠረት የተውጣጡ አባላት እየተሳተፉ ይገኛል፡፡

በማስተዋል አሰፋ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.