Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች በዴንቨር ከተማ ከንቲባ ሚካኤል ቢ ሐንኮክ ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዴንቨር ከተማ ከንቲባ ሚካኤል ቢ ሐንኮክ ከተመራ የልዑካን ቡድን ጋር ተወያይተዋል፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ በዴንቨር ከተማ ከንቲባ ሚካኤል ቢ ሐንኮክ ለተመራ የልዑካን ቡድን በከንቲባ ጽህፈትቤት የአስተዳደሩ የካቢኔ አባላት በተገኙበት አቀባበል አድርገናል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዴንቨር አዲስ አበባ በጀመረው አዲስ የበረራ መስመር የሁለቱን ከተሞች ግንኙነት ለማጠናከር ወደ አዲስ አበባ የመጣው ልዑክ ከከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ጋር መወያየቱንም ጠቁመዋል፡፡

በዚህም የሁለቱን ከተሞች ግንኙነት የሚያጠናክር ፍሬያማ ውይይት መደረጉን ነው የተናገሩት፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.