Fana: At a Speed of Life!

በፓኪስታን በተፈጸመ ጥቃት የ59 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ፓኪስታን ግዛት ፔሻዋር ከተማ መስጊድ ውስጥ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት ቢያንስ የ59 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡

ጥቃት የተፈጸመበት መስጊድ ከፍተኛ ጥበቃ በሚደረግበት የሀገሪቱ ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት አቅራቢያ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

ጥቃቱ በመስጊዱ ቅጥር ግቢ ለጸሎት ተሰብስበው በነበሩ የፖሊስ አባላት ላይ ያነጣጠር እንደነበር ነው የተጠቆመው፡፡

በተፈጸመው ጥቃት ከሞቱት በተጨማሪ 157 በላይ ሰዎች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን÷ እስካሁን ለጥቃቱ ሃላፊነት የወሰደ አካል አለመኖሩ ተገልጿል፡፡

የፖኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሸህባዝ ሻሪፍ÷ በአጥፍቶ ጠፊዎች በመስጊድ ውስጥ የተፈጸመውን ጥቃት በጽኑ ኮንነዋል፡፡

ድርጊቱ ህዝብን በሚጠብቁ የፓኪስታን ፖሊስ አባላት ዘንድ ስጋት ለመፍጠር ያለመ የፈሪ ጥቃት ነው ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.