Fana: At a Speed of Life!

83ኛው የአገው ፈረሰኞች ማህበር በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 83ኛው የአገው ፈረሰኞች ማህበር የምስረታ በዓል በተለያዩ ሁነቶች በእንጅባራ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡

በበዓሉ አከባበር ላይ የፌዴራል እና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች፣ ልዩ ልዩ የኪነ ጥበብ ሰዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል፡፡

በዓሉ “አምራች ፤ ዘማች የአገው ፈረሰኞች ማህበር “በሚል መሪ ቃል እየተከበረ እንደሚገኝ ከዞኑ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የአገው ፈረሰኞች ማኅበር የአገው አባቶች ከሌሎች አባት አርበኞች ጋር በመተባበር የጣልያንን ወራሪ ጦር ዓድዋ ላይ ድል መቀዳጀታቸውን ለመዘከር በየዓመቱ ጥር 23 በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የሚከበር በዓል ነው፡፡

ማኅበሩ በ1932 ዓ.ም ከ30 በማይበልጡ አባላት የተመሰረተ ሲሆን÷ በአሁኑ ወቅት ከ60 ሺህ በላይ አባላት አሉት፡፡

የአገው ፈረሰኞች በዓልን በተባበሩት መንግስታት የትምህርት ፣የሳይንስና ባህል ተቋም (ዩኔስኮ) በማይዳሰሱ ቅርሶች ለማስመዝገብ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ነው ተብሏል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.