Fana: At a Speed of Life!

በዱር እንስሳት እና መኖሪያቸው ላይ ሕገ ወጥ ተግባር የፈፀሙ 65 ግለሰቦች በሕግ እንዲጠየቁ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዱር እንስሳት እና መኖሪያቸው ላይ ሕገ ወጥ ተግባራትን ፈጽመዋል ተብለው ከተጠረጠሩ 111 ሰዎች መካከል በ65 ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላለፈ፡፡

የዱር እንስሳትን መኖሪያ ምቹ ለማድግ በሚከናወኑ ሥራዎች ላይ የደን ጭፍጨፋ፣ ሕገ ወጥ እርሻ፣ ሕገ ወጥ ሰፈራ እና ሕገ ወጥ አደን ተግዳሮት መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ከእንስሳት እና ሰው ግጭት ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ በጅብ ምክንያት የአምስት ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡

ለዱር እንስሳት ጥበቃ በሚደረግባቸው ቦታዎች ደግሞ በተለያዩ ጥብቅ ደኖች እና ፓርኮች አራት ዝሆን፣ ሁለት ጎሽ እና አንድ አንበሳ ተገድለዋል፡፡

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ናቃቸው ብርሌው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ባለፉት ስድስት ወራት 58 ሺህ 800 ጎብኚዎች ባለስልጣኑ የሚስተዳድራቸውን ብሔራዊ ፓርኮች እና የእንስሳስት መጠለያዎች ጎብኝተዋል፡፡

ከዚህም 21 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ገቢ ተገኝቷል ነው ያሉት፡፡

ከጉብኝቱ መዳረሻዎች መካከልም በዋናነት ሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ፣ ባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ፣ ነጭ ሣር ብሔራዊ ፓርክ እና አቢጃታ ሻላ ሐይቆች ብሔራዊ ፓርክ መሆናቸውን ነው ያብራሩት፡፡

ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት 35 ሺህ 411 ጎብኚዎች ፓርኮችን እንደጎበኙ እና ከዚህም 18 ነጥ 8 ሚሊየን ብር እንደተገኘ አስታውሰው፥ የ2015 ዓ.ም የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ዕድገት ማሳየቱን ጠቁመዋል፡፡

ባለስልጣኑ 11 ብሔራዊ ፓርኮችን እና ሁለት የዱር እንስሳት መጠለያዎችን እደሚስያስተዳድር ይታወቃል፡፡

በክልሎች ለሚገኙ የተለያዩ የማህበረሰብ አቀፍ ጥብቅ ስፍራዎች እና ብሔራዊ ፓርኮች ቴክኒካል ድጋፍ እንደሚያደርግም አቶ ናቃቸው ተናግረዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.