Fana: At a Speed of Life!

ተቋማት ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽኑን ሊደግፉት እንደሚገባ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሔራዊ ምክክር ኮሚሽኑን ተቋማት በልዩ ሁኔታ ሊደግፉት እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡

በቅርቡ ወደ ዉይይት እንደሚገባ የተነገረለት ብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን እስካሁን የነበረዉ ሂደትና ቅቡልነቱ መልካም እንደሆነ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸዉ ኮሚሽነሮች ተናግረዋል፡፡

ያለፉ ስብራቶች እንዲጠገኑ ትዉልድም እንዲድን ፈጣን ዉይይት ዛሬም ልዩ አማራጭ ነዉ ያሉት የኮሚሽኑ ዋና ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ÷ ችግሮችን በጊዜ እና በፍጥነት ፈቶ ወደ እንድነት ማምጣት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ኮሚሽነር ዶክተር ዮናስ አዳዬ በበኩላቸው ፥ ዉይይቱ ሲጀመር የሚፈጠሩ እንቅፋቶች እንዳይኖሩ ተቋማት ግንባር ቀደም መሆን አለባቸዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽነሩ አክለውም ፥ ዩኒቨርሲቲዎች፣ መገናኛ ብዙሃንና የሲቪክ ማህበራት ለምክክር ኮሚሽኑ ድጋፍ ለማድረግ ሁሉንም በሮቻቸውን ክፍት የማድረግ ሃላፊነት እንዳለባቸዉም ነው ያነሱት፡፡

ይህ ምክክር የተሳካና ተምሳሌታዊ ይሆናል ብለው እንደሚያምኑ የገለፁት ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ÷ ለዲሞክራሲም መሰረት በመጣል ቀጣዩ ትዉልድም በተሻለ መንገድ እንዲጓዝ ያግዛል ነዉ ያሉት፡፡

በሃይማኖት ወንድራድ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.