Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የሞጆ ወደብና ተርሚናልን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የሞጆ ወደብና ተርሚናልን ገብኝተዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ የወደብና ተርሚናሉን አጠቃላይ እንቅስቃሴ የጉምሩክ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታን ጨምሮ የክልሉ የስራ ኃላፊዎች እና የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሮባ መገርሳ በተገኙበት ነው የጎበኙት፡፡
በጉብኝታቸውም÷ የሞጆ ወደብና ተርሚናል ባለው መሰረተ ልማት፣በሚሰጠው አገልግሎት እና በሚሰራቸው የማስፋያ ስራዎች መደሰታቸውን መግለፃቸውን ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ርእሰ መስተዳድር ሽመልስ በቀጣይም ወደቡን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዙ እና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡
የሞጆ ወደብና ተርሚናል ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው የገቢ ወጪ ንግድ እንደሚያስተናግድ ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.