Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ስለሺ ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛና የአፍሪካ ጉዳይ ቢሮ ም/ ሃላፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 24 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሀመር እና ከአፍሪካ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አምባሳደር ሞሊ ፊ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በሰላም ስምምነቱ አተገባበር ዙሪያ እና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አምባሳደር ስለሺ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

አምባሳደር ሽለሲ የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ የተከናወኑ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስራዎችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በሰላም ስምምነቱ አተገባበር ላይ በቀጣይ ሊኖሩ በሚችሉ ተግዳሮቶች ዙሪያ መምከራቸውን ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.