Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ 2 ቢሊየን ዶላር የሚያወጡ ወታደራዊ ድጋፎችን ለኪየቭ ልታደርግ መሆኑ ተሰማ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 24 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ የረጅም ርቀት ሚሳኤሏን ጨምሮ እስከ 2 ቢሊየን ዶላር የሚያወጡ የተለያዩ የጦር መሣሪያዎችን ለዩክሬን ልታስታጥቅ መሆኑ ተሰማ፡፡

ዋሺንግተን ዩክሬን ለማስታጠቅ ያዘጋጀችው ከምድር የሚወነጨፍ ሚሳኤል እስከ 150 ኪሎ ሜትር ወደ ሩሲያ ግዛት ዘልቆ በመግባት ማደባየት እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

ኪየቭ በቀጣይ ጃቬሊን የተሠኙ የአሜሪካ ፀረ-ታንክ መሣሪያዎች ፣ የተለያዩ የመልክዓ-ምድር ገፅታዎችን በብቃት ተቋቁመው ማለፍ የሚችሉ ተሽከርካሪዎች፣ የተለያዩ መጠን ያላቸውን ሮኬቶች ማስወንጨፊያ እንዲሁም የዓየር ጥቃት በሚፈፀምበት ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውሉ ቁሳቁስን ከአሜሪካ እንደሚቀርብላት ሬውተርስ መዘገቡን አር ቲ አስነብቧል፡፡

ዋሺንግተን ለዩክሬን የምታቀርበው የረጅም ርቀት የሚሳኤል ማስወንጨፊያ ሥርዓት ከዚህ ቀደም ከኔቶ ጋር ሆና ካቀረበችላት የመካከለኛ ርቀት ሚሳኤል ማስወንጨፊያ በሁለት እጥፍ የሚልቅ ርቀት መሸፈን የሚችል ዐቅም አለው ተብሏል፡፡

ባለፈው ሳምንት አሜሪካ ለዩክሬን ኤም 1 አብራምስ የተሰኘውን ታንክ መላክ የሚያስችለውን እቅድ ማጽደቋ ይታወሳል።

ሩሲያም አሜሪካ የምታደርገው ድጋፍ ጦርነቱን የሚያራዝምና ዓለም አቀፍ ውድመት የሚያስከትል ነው ስትል ማስጠንቀቋ ይታወሳል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.